ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት

ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የሚገኝበት ቦታ በቀድሞ ወረዳ 22 ቀበሌ 07 ቤት ቁጥር ከ107-111 ከፊሊፕስ ህንፃ ጎን

የሚያስተዳድራቸው ቤቶች ብዛት 3137

ስልክ ቁጥር :- 0115-15-45-49

 

የምንሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች

 1. አዲስ ለሚከራዩ ቤቶች ውል መሙላት
 2. ለመንግስት ተሿሚዎች ቤት ከኪራይ ነፃ ሲመደብ በወቅቱ ቤት ማስረከብ
 3. የቤቶችን ውል በየአመቱ ማደስ
 4. የስም ዝውውርና የዘርፍ ለውጥ ፈቃድ መስጠት
 5. የቤቶችን ኪራይ በየወሩ መሰብሰብ
 6. ለአፓርታማዎች የፅዳትና ጥበቃ አገልግሎት መስጠት
 7. በቤቶች ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን መከላከል
 8. ለቤቶች የጥገና አገልግሎት መስጠት
 9. ጥገና ፍቃድ መስጠትና ሌሎች ተግባራት ናቸው፡፡

ውልን ለማደስ ሲመጡ

 1. የቅርብ ጊዜ 2 ፎቶ ግራፍ
 2. መጨረሻ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ
 3. ቤቱ መኖርያ ከሆነ በቤት ቁጥር የወጣና የታደሰ መታወቅያ
 4. ተካራይ ያገባ/ች ከሆነ/ች ህጋዊ የጋብቻ ሴርቲፍኬት በማቅረብ የትዳር አጋርን ማስመዝገብ
 5. የተጠቀመበትን የማብራትና የውሃ ክፍያ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፡፡

ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ኮርፖሬሽኑ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ የተከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 3 ቀን 2012 በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ጊቢ በመገኘት አከበሩ፡፡

በኦዲት ፅንሰ ሃሳብና አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ዋና ባለሙያዎች በውስጥ ኦዲት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በራስ ሆቴል ተሰጠ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከ8 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች የመደበኛ ወርሃዊ ኪራይ ፣ ከውዝፍ ኪራይ፣ ከልዩ ልዩ ገቢ እና ከውል እድሳት ፣ከፈረሱ ቤቶች የካሳ ክፍያ ፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ዘርፍ አማካኝነት ከብሎኬት ሽያጭ፣ ከጠጠር ሽያጭ፣ ተገዝተው ከሚሸጡ ዕቃዎች ፤ ከትራንስፖርት አገልግሎት እና ከመጋዘን ኪራይ እንዲሁም ከወለድ ፤ ከኪራይ ዋስትና ተቀማጭ እና ቅድመ ክፍያ በድምሩ 818.76 ሚሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከኔዘርላንድ እና ከሌሎች ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ጋር ተወያየ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከኔዘርላንድና ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ የምርምርና እና ዲዛይን የባለሙያዎች ቡድን ጋር ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የኮርፖሬሽኑን መስሪያቤቶችና የቤት ግንባታ ሳይት ጎበኘ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ.ም የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መስሪያ ቤቶችንና የግንባታ ሳይትን ጎበኘ፡፡

የዋና ሥራ አስፈጻሚ መልዕክት የዋና ሥራ አስፈጻሚ መልዕክት

የዋና ሥራ አስፈጻሚ መልዕክት

ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሠለፍ የያዘችውን ራዕይ ለማሣካት ፈርጀ ብዙ ሀገራዊ ልማቶች በረጅምና በአጭር ጊዜ ዕቅድ ነድፋ በማከናወን ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡

የአስተያየት መስጫ ፎርም የአስተያየት መስጫ ፎርም

እባኮዎ አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ለሚሰጡን ጠቃሚ አስተያየት እናመሰግናለን፡፡

መረጃውን ያስገቡ
መረጃውን ያስገቡ
መረጃውን ያስገቡ
Text to Identify Refresh CAPTCHA Refresh CAPTCHA

የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል

በተደጋጋሚ የተጎበኙ ገጾች በተደጋጋሚ የተጎበኙ ገጾች

ኮርፖሬሽኑ ከ8 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች የመደበኛ ወርሃዊ ኪራይ ፣ ከውዝፍ ኪራይ፣ ከልዩ ልዩ ገቢ እና ከውል እድሳት ፣ከፈረሱ ቤቶች የካሳ ክፍያ ፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ዘርፍ አማካኝነት ከብሎኬት ሽያጭ፣ ከጠጠር ሽያጭ፣ ተገዝተው ከሚሸጡ ዕቃዎች ፤ ከትራንስፖርት አገልግሎት እና ከመጋዘን ኪራይ እንዲሁም ከወለድ ፤ ከኪራይ ዋስትና ተቀማጭ እና ቅድመ ክፍያ በድምሩ 818.76 ሚሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል፡፡ በዚህም ኮርፖሬሽኑ ለበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ካቀደው 99.8 በመቶውን ማሳካቱን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
የ2011 በጀት ዓመት አጠቃላይ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸጸም ካለፉት ሁለት አመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2009 በጀት ዓመት አጠቃለይ ገቢ ብር 408.1 ሚሊየን ፤በ2010 በጀት አመት ብር 367 ሚሊየን ሲሆን በ2011 በጀት አመት ወደ ብር 818.77 ሚሊየን ከፍ ሊል ችሏል፡፡ በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ሊጋኝ የቻለው ለአመታት እየተሞከረ ሳይሳካ የቆየውንና የኮርፖሬሽኑን ሥራ በብዙ ሊደግፍ የሚችል የንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን ማሻሻያ ጥናት በማከናወን ከ97.5 % በላይ የንግድ ቤት ተከራዮች በማሻሻያው መሰረት ውል እንዲፈጽሙ በመደረጉ እና የቀድሞው የህንፃ አቅራቢዎች ድርጅት ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመዋሃዱ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ ገቢውን ለማሳደግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን ገንዘብ በከተማዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የቤት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ባለመው የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል የበጀት ዓመቱ ሪፖርት አመላክቷል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በ2011 በጀት ዓመት የተቋሙን ወጪ ለመቀነስ በተደረገው ጥረት በርካታ መጠን ያለውን የገንዘብ መጠን ለማዳን የተቻለ ሲሆን ከነዚህም መካከል የወጪ መጋራት ሥርዓት በመዘርጋት፣ ከደንበኞች ጋር በመወያየትና ስምምነት ላይ በመድረስ በአፓርታማ የሚሰጡ የጥገና፣ የጥበቃ፣ የፅዳት፣ የግቢ ማስዋብና ሌሎች ሥራዎች በማህበራት ወጪና በወጪ መጋራት በተሳትፎ እንዲከናወኑ በማድረግ የብር 17.46 ሚሊዮን ብር የተቋሙን ወጪ መቀነስ ተችሏል፡፡
ደንበኞችን በወጪ ቆጣቢ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የተቋሙን ወጪ በተሻለ መጠን ለመቀነስ እንዲቻል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ የ40/60 ቤቶች በውስጥ አቅም 98 ኪችን ካቢኔት በመስራት በግምት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መቀነስ ተችሏል፡፡