ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

ኮርፖሬሽኑ ለተቋሙ ሰራተኞች የ“IFRS” ስልጠና መስጠት ጀመረ

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዓለም አቀፍ የፋናንስ ሪፖርት ደረጃዎች /IFRS/ አሰራርን በተቋሙ ውስጥ ለመጀመር የሚያስችልና ከግንቦት 05 እስከ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው ካፕላን (KAPLAN) የስልጠናና አማካሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተባለው ተቋም እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ 62 ሰራተኞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በቀጣይ ዙሮች በኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ለሚገኙ ሰራተኞች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡