ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

ኮርፖሬሽኑ ከ8 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች የመደበኛ ወርሃዊ ኪራይ ፣ ከውዝፍ ኪራይ፣ ከልዩ ልዩ ገቢ እና ከውል እድሳት ፣ከፈረሱ ቤቶች የካሳ ክፍያ ፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ዘርፍ አማካኝነት ከብሎኬት ሽያጭ፣ ከጠጠር ሽያጭ፣ ተገዝተው ከሚሸጡ ዕቃዎች ፤ ከትራንስፖርት አገልግሎት እና ከመጋዘን ኪራይ እንዲሁም ከወለድ ፤ ከኪራይ ዋስትና ተቀማጭ እና ቅድመ ክፍያ በድምሩ 818.76 ሚሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል፡፡ በዚህም ኮርፖሬሽኑ ለበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ካቀደው 99.8 በመቶውን ማሳካቱን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
የ2011 በጀት ዓመት አጠቃላይ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸጸም ካለፉት ሁለት አመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2009 በጀት ዓመት አጠቃለይ ገቢ ብር 408.1 ሚሊየን ፤በ2010 በጀት አመት ብር 367 ሚሊየን ሲሆን በ2011 በጀት አመት ወደ ብር 818.77 ሚሊየን ከፍ ሊል ችሏል፡፡ በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ሊጋኝ የቻለው ለአመታት እየተሞከረ ሳይሳካ የቆየውንና የኮርፖሬሽኑን ሥራ በብዙ ሊደግፍ የሚችል የንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን ማሻሻያ ጥናት በማከናወን ከ97.5 % በላይ የንግድ ቤት ተከራዮች በማሻሻያው መሰረት ውል እንዲፈጽሙ በመደረጉ እና የቀድሞው የህንፃ አቅራቢዎች ድርጅት ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመዋሃዱ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ ገቢውን ለማሳደግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን ገንዘብ በከተማዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የቤት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ባለመው የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል የበጀት ዓመቱ ሪፖርት አመላክቷል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በ2011 በጀት ዓመት የተቋሙን ወጪ ለመቀነስ በተደረገው ጥረት በርካታ መጠን ያለውን የገንዘብ መጠን ለማዳን የተቻለ ሲሆን ከነዚህም መካከል የወጪ መጋራት ሥርዓት በመዘርጋት፣ ከደንበኞች ጋር በመወያየትና ስምምነት ላይ በመድረስ በአፓርታማ የሚሰጡ የጥገና፣ የጥበቃ፣ የፅዳት፣ የግቢ ማስዋብና ሌሎች ሥራዎች በማህበራት ወጪና በወጪ መጋራት በተሳትፎ እንዲከናወኑ በማድረግ የብር 17.46 ሚሊዮን ብር የተቋሙን ወጪ መቀነስ ተችሏል፡፡
ደንበኞችን በወጪ ቆጣቢ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የተቋሙን ወጪ በተሻለ መጠን ለመቀነስ እንዲቻል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ የ40/60 ቤቶች በውስጥ አቅም 98 ኪችን ካቢኔት በመስራት በግምት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መቀነስ ተችሏል፡፡