ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ተገመገመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ2ዐ1ዐ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት ከሰኔ 29 እስከ ሃምሌ 01 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ/ም አዳማ በሚገኘው ኩርፍቱ ሪዞርት መሰብሰቢያ አዳራሽ ገመገመ፡፡

ግምገማው በዋናነት ያተኮረው የኮርፖሬሽኑ የቤት ልማት፣ የቤት አስተዳደር፣የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፎች፣ የለውጥና መልካም አስተዳደር እና ለዋና ሥራ አስፈፃሚ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎች በ2010 በጀት ዓመት የከወኑዋቸው ተግባራት ገምግመው፤ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብዓት እንዲሆንና ማሻሻያ ለሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ አቅጣጫ ለመስጠት ጭምር ታስቦ መድረኩ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡