ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ18,153 የቤት ተከራዬች በድጋሜ 50 በመቶ የግንቦት ወር ቅናሽ አደረገ፡፡


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ18,153 የቤት ተከራዬች በድጋሜ 50 በመቶ የግንቦት ወር ቅናሽ በማድረግ ኮረናን ለመከላከል ያበረከተው አስተዋጾኦ 130 ሚሊዬን ብር ደረሰ፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የሚገኙ 18,153 የመኖሪያና የድርጅት ቤቶች ተከራይ ደንበኞች የኮቪድ 19 የኮረና ቫይረስ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የፈጠረባቸውን ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ በመረዳት የሚያዚያ ወር የክራይ ቅናሽ ሲያደርግ በቀጣይም የበሽታው ሁኔታና የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል በየወሩ እየገመገመ ቅናሽ ለማድረግ በገባው ቃል መሰረት አሁን ላይ ያለው የበሽታው ሁኔታ በሥራ ላይ እየፈጠረ ያለው ተፅእኖ በከፊል የቀጠለ መሆኖን በመገንዘብ የግንቦት ወር የክራይ ክፍያ በ50 በመቶ ለተከራይ ደንበኞች ተቀንሶላቸው በተፅእኖው እንዳይጎዱ ተወስኗል፡፡ በዚህም ኮርፖሬሽኑ በግንቦት ወር ሊሰበስበው ካቀደው 120 ሚሊዮን ብር 60 ሚሊዬን ብር የሚያሳጣው ይሆናል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የኮቪድ 19 የኮረና ቨይረስ ወረርሽኝ የሀገራችን ስጋት ከሆነበት ባለፋት ሶስት ወራት ውስጥ በሽታውን ለመከላከል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የላቀ አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን ለኮቪድ 19 ድጋፍ አሰባሳቢ ብሔራዊ ኮሚቴ 10 ሚሊዬን ብር በማበርከት፣ ከተከራይ ደንበኞች የሚሰበሰበውን የሚያዚያ ወር ክፍያ ለእያንዳንዱ ተከራይ ሃምሳ በመቶ ቅናሽ በማድረግ 60 ሚሊዬን ብር በማስቀረት እንዲሁም በተመሳሳይ ከግንቦት ወር ሊሰበሰብ ከታቀደው ለእያንዳንዱ ተከራይ 50 በመቶ ተቀናሽ በማድረግ ሊያገኝ የነበረው 60 ሚሊዩን ብር በመተው ኮርፖሬሽኑ እስካሁን በድምሩ 130 ሚሊዬን ብር ኮረና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ አበርክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ባደረገው የ50 በመቶ የወርሃዊ የኪራይ ክፍያ ቅናሽ 11,860 የመኖሪያና 6,293 የድርጅት ቤቶች በቀጥታ ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን ከነዚህም ወርክሾፖች፣ ሱቆች፣ መጋዘኖች፣ አዳራሾች ፣ሆቴሎች ፣ የኤሌክትሮኒክስ መሸጫዎች፣ ሸቀጣሸቀጦች፣ ዳቦ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች ፣በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶች፣ ቢሮዎች እና በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች ናቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ የኮቪድ 19 የኮረና ቫይረስ ለመከላከል እያደረገው ያለውን ርብርብ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸው ስራዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳይፈጥር ቁልፍና አበይት ተግባራትን ለይቶ ስራዎቹን በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል እንደሀገር የተጀመረዉን ሪፎርም በተቋሙ እውን እንዲሆን ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደንብ ቁጥር 398/2009 የተለያዩ ተግባርና ሃላፊነቶች ተሰጥተዉት በራሱ ገቢ እንዲተዳደር የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡