ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

ኮርፖሬሽኑ ለገበታ-ለሃገር ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ብር አበረከተ

የፌዴራል ቤቶቸ ኮርፖሬሽን እንደ ሃገር የተጀመረዉን ሪፎርም ከግብ ለማድረስ እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ እና እየተመዘገበ ያለዉን ተስፋ ሰጪ ውጤት የድርሻዉን ለማበርከት ለሃገራዊ የልማት ጥሪዎች ምላሽ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በቅርቡ ለገበታ-ለሃገር ፕሮጀክቶች ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን በድምሩ 10 ሚሊዮን ብር ማበርከታቸውን ይታወሳል፡፡ “ያለ ሁለንተናዊ ተሳትፎና የጋራ ትብብር ሃገር አይገነባም” የሚል እምነት የሰነቀው የፌዴራል ቤቶቸ ኮርፖሬሽን አሁንም በድጋሜ በኮርፖሬሽኑ ሥም ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለገበታ-ለሃገር ፕሮጀክቶች ግንባታ አበርክቷል ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው የገንዘብ አስተዋጽኦዎች ለመቄዶኒያ የአረጋዊያን መኖሪያ ግንባታ 5 ሚሊዮን ብር፣ የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል እየተደረገ ላለው ሀገራዊ ርብርብ 10 ሚሊዮን ብር፣ ባለፉት 6 ወራት የኮርፖሬሽኑ ተከራይ ደንበኞች 50% የቤት የኪራይ ክፍያ እንዲቀነስላቸው በማድረግ 400 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለገበታ-ለሃገር የተሰጠዉን 20 ሚሊዮን ብር ተጨምሮ በድምሩ 435 ሚለዮን ብር ገደማ ወጪ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ በሃገሪቱ ካሉት ተቋማት ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ቀዳሚ ቦታዉን ይዞ ይገኛል፡፡