ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ኮርፖሬሽኑ አሥር ሚሊዮን ብር አበረከተ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ወደ አገራችን በቅርቡ የተሰራጨው ኮቪድ19 የኮረና ቫይረስ ለመግታትና ለመመከት እየተደረገ ያለዉን ሀገርአቀፍ ርብርብ የሚረዳ አሥር ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የኮቪድ19 ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ያቀረበዉን ሀገርአቀፍ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በሰላም ሚኒስቴር ለርክክብ ሥነ-ስርዓቱ የተገኙ ሲሆን ክቡር አምባሳደር ምስጋናው የኮቪድ19 ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ከሚቴ አባል ኮርፖሬሽኑ ያበረከተዉን የአሥር ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተረክበዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ባስተላለፉት መልእክት ኮቪድ19 የኮረና ቫይረስ ዓለምን ያለ ምንም ልዩነት እየፈተናት እንደሚገኝ አውስተው አገራችን ከዚህ አስከፊ የቫይረስ ስርጭት ለመታደግ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ታዋቂ ግለሰቦች እንደ ሀገር የገጠመንን ፈተና ለመሻገር የላቀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ የዚህ ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት በተሞላበት ራሱን እንዲጠብቅ፣ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ከጤና ሚኒስቴር እና ከታማኝ ሚዲያዎች በሚገኙ መረጃዎች ብቻ ተጠቅሞ ሥርጭቱን በመግታት የድርሻዉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
ኮቪድ19 የኮረና ቫይረስ ከአገራችን እስኪጠፋ ድረስ መንግስት በሚያቀርበው ጥሪ መሰረት የኮርፖሬሽኑን ድጋፍ ቀጣይ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው አክለው ገልጸዋል፡፡