ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ኮርፖሬሽኑ አረንጓዴ አሻራውን አኖረ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እና አመራሮች ከተከራይ ደንበኞቹ በጋራ በመሆን ከአስር ሺህ በላይ አገርበቀል ዛፎችና ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ተክሎች በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪፓርክ፣ በቦሌ አራብሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና በኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ላይ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢ ሥነ-ምህዳርን መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ የድርሻውን ለመወጣት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የአንጓዴ አሻራውን ማስረፉን ገልጸዋል፡፡
የተተከሉት ችግኞች ዘላቂነት በላው መንገድ የመንከባከብ ሥራው እንደሚቀጥል አክለው የገለጹ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ የዘንድሮውን መርሀግብር ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የችግኝ ተከላ መርሀግብር መካሄዱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታውሰዋል፡፡