ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ኮርፖሬሽኑ በስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሥነምግባር ፅህፈት ቤት ከኮርፖሬሽኑ የተለያዩ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ለተዉጣጡ 50 ባለሙያዎች ጥቅምት 27/2012 ዓ.ም በራስ ሆቴል ስልጠና ሰጠ፡፡

በሥነ ምግባር ፅንሰ ሐሳብ፣ በሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች እና በአመለካከት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች የተሰጡ ሲሆን የስልጠናው ዓላማ በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የተጀመረውን ሙስናን የመከላከል ተግባር እና ሥነምግባርን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማገዝ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡