ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች ህዳር 04 ቀን 2012 ዓ.ም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን የሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

የኮርፖሬሽኑ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎትና ቅሬታ ማስተናገጃ ዳይሬክቶሬቶች በጋራ በመሆን በራስ ሆቴል ባዘጋጁት ስልጠና 103 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ፣ በኮርፖሬሽኑ የዜጎች ቻርተር እና የቅሬታ ማንዋል ረቂቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡