ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

ኮርፖሬሽኑ ከኔዘርላንድ እና ከሌሎች ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ጋር ተወያየ

ኮርፖሬሽኑ ከኔዘርላንድ እና ከሌሎች ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ጋር ተወያየ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከኔዘርላንድና ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ የምርምርና እና ዲዛይን የባለሙያዎች ቡድን ጋር ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከኔዘርላንድ ዴልፉት ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጵያ አርክቴክቸሮች ማህበር፣ ከኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ተቋማት ከተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ጋር የኮርፖሬሽኑን የቀጣይ አራት ዓመታት ዘለቄታ ያለውና አዋጭ የቤቶች ልማት እና የሙከራ የመኖሪያ መንደር ምስረታን የሚመለከት ጥናት ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ የሚያስገነባቸው የጋራ የመኖሪያ መንደር ዉጤታማና ስኬታማ ሥራ መስራት እንዲቻልና ግንባታው በታቀደዉ መሰረት እንዲከናወን ከባለሙያዎች ቡድን ጋር የጋራ ሥራዎች እንደሚሰሩ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ በተያያዘም የኔዘርላንድ መንግስት በኮርፖሬሽኑ የግንባታ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ በሚችልባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት መደረጉ ታውቋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ በኮርፖሬሽኑ የግንባታ ሳይቶች ላይ በመዘዋወር የመስክ ምልከታም አካሂዷል፡፡