ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃ አተገባበር ላይ ውይይት ተካሄደ


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተቋሙን የፋይናንስ አሰራር በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃ (IFRS) መሠረት ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት አባላት ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃ (IFRS) አሰራር በኮርፖሬሽኑ ውስጥ ተግባራዊ በማድረግ የተቋሙን የፋይናንስ አሠራር ለማዘመን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፋይናንስ አማካሪ ድርጅት ጋር መክረዋል፡፡