ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በንግድ ቤቶች ኪራይ ተመን ማሻሻያ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከደንበኞችና ከጋዜጠኞች ጋር በንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን ማሻሻያ ዙሪያ ህዳር 4 እና 5 ቀን 2011 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል የኮርፖሬሽኑ የንግድ ቤቶች የኪራይ ተመን ለረጅም አመታት ሳይከለስ የቆየ ሲሆን ከግሉ ዘርፍ ጋር ሲነጻጸር ደግሞ ሰፊ ልዩነት እያመጣ በመሆኑ ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ ሥርዓትን እየፈጠረ እንደሚገኝ በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከንግዱ ማህበረሰብና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታ እየቀረበ እንደሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኪራይ ተመን ማሻሻያው በጥናት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የንግድ ቤቶች የሚገኙበት አካባቢ፣ የቤቶቹ ስፋት እና የሚገኙበት ደረጃ ባገናዘበ ሁኔታ አግባብነት ያለው ማሻሻያ እንደሚደረግ አብራርተዋል፡፡ የኪራይ ተመን ማሻሻያው ዙሪያ የተጀመሩና አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በ2011 በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡