ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ አደረገ::

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመቄዶኒያ የአረጋዉያንና የአእምሮ ህሙማን የበጎ አድራጎት ድርጅት 250 ሺህ ብር ግምት ያላቸውን አለባሳትና ጫማዎች መጋቢት 22/2010 ዓ.ም ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፍ በማበርከቱ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው የሚለውን የድርጁትን መሪ ቃል በመጥቀስ ኮርፖሬሽኑ ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታው ለመወጣት ደጋፍ ለሚሹ አካላት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግና ለወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ መቄዶኒያ የአረጋዉያንና የአእምሮ ህሙማን የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ ለሚሹ 1 ሺህ 500 ወገኖች መጠልያ፣ህክምና፣ምግብና አልባሳት እንደሚያቀርብ በመቄዶኒያ የአረጋዉያንና የአእምሮ ህሙማን የበጎ አድራጎት ድርጅት የአረጋውያን ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተከስተ አብርሀም ከገለጹ ብኃላ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ይህ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደቀጥልና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሰራተኞችም ድርጅቱን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርቧል፡፡