ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

የስራ ውል ስምምነት ተፈረመ

የፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ከተቀባና ጓደኞቹ የንብረት ዋጋ ግመታና አስተዳደር የተወሰነ የግል ማህበር ጣምራ አኪዩት ኢንጂነሪነግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የቤቶችና ተያያዥ የሲቪል ስራዎች ዋጋ ግመታ ስራ ለማከናወን ረቡዕ ሚያዝያ 3, 2010 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የዋና ስራ አስፈጻሚ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ኮርፖሬሽኑን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ሲሆኑ በአማካሪ ድርጅቱ በኩል ደግሞ የተቀባና ጓደኞቹ የንብረት ግመታና አስተዳደር መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ተቀባ ብርሃኑ ናቸው፡፡ የስምምነቱ ዋና ዓላማ የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የሃብት መጠን ለማወቅና በአግባቡ ለማስተዳደር እንዲሁም ከቤት ልማት ስራ ጋር በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ለሚያደርገው የብድር ስምምነት ምቹ መደላድል ለመፍጠር እንደሆነ ታውቋል፡፡ የዋጋ ግመታው የሚሰራላቸው በአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተሞች የሚገኙ 18,445 ቤቶች ሲሆኑ የግመታ ስራው በሁለት ምዕራፍ የተከፋፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያው የግመታ ምዕራፍ እስከ ሰኔ 30,2010 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚህ ምዕራፍ በአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርንጫፍ ሁለት ስር የሚተዳደሩ 1,123 ቤቶች፤በቅርንጫፍ ሶስት ስር ያሉ 2,230 ቤቶች እንዲሁም በልዩ ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኙ 508 ቤቶችን በድምሩ የ3,861 ቤቶች ንብረት ግመታ ይሰራል፡፡ የቀሪዎቹ 14,584 ቤቶች ስራ በሁለተኛው ምዕራፍ እስከ መስከረም 30, 2011 ዓ.ም እንደሚከናወን በስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ የተቀባና ጓደኞቹ የንብረት ግመታና አስተዳደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጣምራ አኪዩት ኢንጂነሪነግ በንብረት ግመታና አስተዳደር የማማከር ስራ በቂ ልምድ ያለው ሲሆን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ባንክሮች ማህበር፤ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ስቲል ማምረቻ ንብረቶችና ወዘተ.. ሃብት ግመታ መስራቱ ታውቋል፡፡


የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች