የኮርፖሬሽኑ ታሪካዊ አመጣጥ የኮርፖሬሽኑ ታሪካዊ አመጣጥ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቀደም ሲል የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 58/1968 ተቋቁሞ በልማት ድርጅትነት ሲተዳደር ከቆየ በኋላ ከ2000 ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 555/2000 መሠረት የመንግሥት ቤቶች ኤጄንሲ በሚል ስያሜ ወደ ፌዴራል አስፈፃሚ መስሪያ ቤት ተቀይሮ ሥራውን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ይህ አደረጃጀት በወቅቱ የፌዴራል መንግሥት ንብረት የሆኑ ቤቶችን በአግባቡ ለማስተዳደርና ለቤቶቹ የሚደረገውን ጥበቃና እንክብካቤ ለማሻሻል ታስቦ የተደረገ ቢሆንም የሚፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ድርጅቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆኗል፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ በየጊዜው የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ተግባራዊ ቢደረግም ተቋሙ በመሰረታዊነት ከችግሩ መላቀቅ እንዳልቻለ በተደጋጋሚ በተደረገው ጥናት እና የአፈጻጸም ግምገማ ማየት ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል ተቋሙ ቤት መገንባት ቢያቋርጥም አዲስ ቤት ከመገንባት ባልተናነሰ ከፍተኛ ሙያ ያለው የሰው ሃይልና ወጪ የሚጠይቅ የመከላከል እና የተመላላሽ ጥገና ሥራዎችን የሚያከናውን በመሆኑ አሁን ያለው አደረጃጀት የጥገና ሥራዎችን በአግባቡ በማከናወን ላይ የራሱ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠር ችሏል፡፡

የሚኒስትሮች ም/ቤት ጥር 26 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሳበ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እንዲቋቋም ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ኮርፖሬሽኑ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 398/2009 ተቋቁሟል፡፡ በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ የቀድሞ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ መብቶችና ግዴታዎች የተላለፉለት ሲሆን የቤት ልማት እና ተዛማጅ ዓላማዎች ተሰጥተውት የተቋቋመ በመሆኑ ይህንን ተልእኮ መሸከም የሚችል የተቋማዊ አደረጃጀት (መዋቅር)፣ የሥራ ክፍሎች ዋና ዋና ተግባራት፣ የሰው ኃይል ዕቅድ፣ የሥራ መደቦች ዝቅተኛ የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ እንዲሁም የሥራ መደቦች ደረጃና የደመወዝ ስኬል ጥናት አከናውኗል፡፡

የኮርፖሬሽኑ አደረጃጀት አንድ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ሶስት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ማለትም የቤት አስተዳደር ዘርፍ፣ የቤት ልማት ዘርፍና የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ የያዘ ነው፡፡ አደረጃጀቱ ዳይሬክቶሬቶች፣ ፅ/ቤቶችና አገልግሎት ሲኖሩት በዳይሬክቶሬቶችም ስር ተቀራራቢ ሥራዎችን የሚመሩ ቡድኖች ተደራጅተዋል፡፡ በአጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ አደረጃጀት 16 ዳይሬክቶሬቶች፣ 6 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ 4 ጽ/ቤቶች፣ አንድ አገልግሎት እና 64 ቡድኖች ያሉት ሲሆን 1492 የሚደርሱ ሠራተኞችን አካቶ ይዟል፡፡

የ40 ዓመት ታሪክ ለማወቅ

ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ኮርፖሬሽኑ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ የተከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 3 ቀን 2012 በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ጊቢ በመገኘት አከበሩ፡፡

በኦዲት ፅንሰ ሃሳብና አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ዋና ባለሙያዎች በውስጥ ኦዲት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በራስ ሆቴል ተሰጠ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከ8 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የ2011 በጀት ዓመት ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች የመደበኛ ወርሃዊ ኪራይ ፣ ከውዝፍ ኪራይ፣ ከልዩ ልዩ ገቢ እና ከውል እድሳት ፣ከፈረሱ ቤቶች የካሳ ክፍያ ፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ዘርፍ አማካኝነት ከብሎኬት ሽያጭ፣ ከጠጠር ሽያጭ፣ ተገዝተው ከሚሸጡ ዕቃዎች ፤ ከትራንስፖርት አገልግሎት እና ከመጋዘን ኪራይ እንዲሁም ከወለድ ፤ ከኪራይ ዋስትና ተቀማጭ እና ቅድመ ክፍያ በድምሩ 818.76 ሚሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከኔዘርላንድ እና ከሌሎች ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ጋር ተወያየ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከኔዘርላንድና ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ የምርምርና እና ዲዛይን የባለሙያዎች ቡድን ጋር ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የኮርፖሬሽኑን መስሪያቤቶችና የቤት ግንባታ ሳይት ጎበኘ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ.ም የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መስሪያ ቤቶችንና የግንባታ ሳይትን ጎበኘ፡፡

የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች