ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 11ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመላው ሀገሪቱ "ሰንደቅ ዓላማችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን" በሚል መሪ ቃል ለ11ኛ ጊዜ የተከበረውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ እና በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች አከበረ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለ ብርሃን ዜና በዋናው መስሪያቤት የባንዲራ የመስቀል ሥነስርአት የፈጸሙ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በወታደራዊ ሥነስርአት ለዝግጅቱ ልዩ ድምቀት መስጠታቸውን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

በዋናው መሥሪያቤትና በሁሉም ቅርንጫፍ መስሪያቤቶች የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር በመዘመር እንዲሁም የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነስርአት በመፈጸም ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አክብረዋል፡፡


የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች