ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች በስትራቴጂክ እቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሥሩ ለተዋቀሩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በስትራተጂክ እቅድ ዝግጅት ላይ ያተኮረና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና ከጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በራስ ሆቴል መስጠት ጀመረ፡፡

በሁለት ዙሮች በሚሰጠው እና እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሚቆየው ስልጠና ላይ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ተወካዮቻቸው እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በኮርፖሬሽኑ ስትራቴጂክ ኘላኒንግና ቢዝነስ ዴቨሎኘመንት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

አሰልጣኞቹ ከቀድሞ የመንግስት ልማት ድርጅት የተጋበዙ ባለሙያዎች ሲሆኑ ለትርፋማነት የተቋቋሙ ተቋማትን የሚያግዙ በስትራቴጅክ ዕቅድ ትርጉም፣ ገጽታዎች ፣ ሂደቶች እንዲሁም የድርጅት ውጤታማነት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች ተሰጥተዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት ስትራቴጂክ ዕቅድ አዘገጃጀትና ዘዴዎች፣ የዕቅድ ይዘቶች፣ የተቋም ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች አነዳደፍ ዙሪያ ማብራሪያዎች ተሰጥተው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡


የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች