ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

ኮርፖሬሽኑ የቤቶች ግንባታ ሊጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ነው

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤቶች ልማት ዘርፍ በሶስት ዓመታት ሊገነባቸው ካቀዳቸው 16 ሺህ ቤቶች መሀከል በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ የ3 ሺህ 200 ቤቶች ግንባታ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በዚሁ መሰረት ከኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ለቤት ልማት ሊውሉ ይችላሉ ተብለው በተለዩ 21 ቦታዎች ላይ ከአስር ወለል በላይ የሚይዙ ህንጻዎችን ለመገንባት የፕላን ስምምነት መወሰዱ ተገልጿል፡፡ የፕላን ስምምነት በተገኘባቸው 21 ቦታዎች ላይ የሚገኙ ተከራዮች በአፋጣኝ ተለዋጭ ቤት ሰጥቶ የማስነሳትና የኪራይ ውል የማቋረጥ ስራ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በኩል እየተከናወነ ይገኛል፡፡ እስከአሁን በተደረገው እንቅስቃሴም 8 ቦታዎች (2.8 ሄክታር) መሬት ከነዋሪዎች ነፃ መደረጉም ታውቋል፡፡ በቀጣይ ከተቋሙ ጋር ይዋሀዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የህንፃ ዕቃዎች አቅራቢ ድርጅት ይዞታ ስር የሚገኙ 5 ቦታዎች (5.1 ሄክታር) በመለየት ከማስተር ፕላን አጠቃቀም አንጻር ተግባቢነታቸውን የመፈተሽ ስራ እንዲሁም ተቋሙ በይዞታዎቹ ላይ የፕላን ስምምነት መጠየቁ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተበታተነ ሁኔታ የሚገኙና ለታቀደው የግንባታ አገልግሎት ለማዋል የሚያስቸግሩ ሰባ አንድ የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች በመዘርዘር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ተመጣጣኝ ቦታ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የቤት ልማት ርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ግሩም ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤት ልማት ፕሮግራሙ ተጨማሪ ቦታ ማግኘት እንዲቻል በኮርፖሬሽኑ ጥያቄ ቀርቦ ተገቢው ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለው ገልፀዋል፡፡ ከዲዛይን ዝግጅትና ጥናት ጋር ያይዞ ከዚህ በፊት በተለያየ አካላት ከተዘጋጁ ሰባት ታይፖሎጂዎች ውስጥ ከፕሮግራሙ ጋር ሊሄዱ የሚችሉትን የመለየት ስራ በመስራት አራት ታይፖሎጂዎች የመምረጥና በቀጣይ ማሻሻያ /ክለሳ/ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን የመለየት ስራ እንደተከናወነ ታውቋል፡፡ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ ይዞታዎች የተለያየ የቦታ አቀማመጥና መጠን ያላቸው በመሆኑና በተመረጡ አራት ታይፖሎጂዎች ወደ ግንባታ ለመግባት የሚያስቸግር ሁኔታ ላለባቸው ቦታዎች አዳዲስ ዲዛይኖች እንደ ቦታው ሁኔታ ለማሰራት በተመረጡ የአማካሪ ድርጅቶች ስራው መጀመሩ ተገልጿል፡፡


የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች